የመጨረሻው ዘመንና የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት

የመጨረሻው ዘመን ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመንና የነገሮች ጅማሬ እንዳለው ሁሉ የዘመንና የነገሮች ፍፃሜ ደግሞ እንዳለው ያስረዳናል። ስለዚህ በዘመን ፍፃሜ ሊሆኑ ስለተቃረቡ እውነቶች በዝርዝር መረዳቱ ከመሰረታዊ የክርስትና እምነታችን አንዱና ዋናው ነገር ስለሆነ ይህንን ማወቅ የማንኛውም አማኝ ግዴታና የቤተ ክርስቲያንም ሃላፊነት ነው። ስለመጨረሻው ዘመን ስንመለከት ልናተኩርባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተሉት ተገልፀዋል፦

1. ዳግም ምፅዓት

2. የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ

3. የመምጣቱ ምልክቶች

4. ታላቁ የመከራ ዘመን

5. የሙታን ትንሳኤና የነጭዙፋን ፍርድ

6. የዘላለም ሕይወት

የጌታ ዳግም ምፅዓት ፦ የጌታን ዳግም ምፅዓት የሚጠባበቁትም ሆነ በመምጣቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት ዳግም ተወልደው የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆኑቱ ብቻ ናቸው።

የምፅዓቱ ተጠቃሚዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በጥቂቱ ስንመለከት፦

ሀ. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ትንቢታዊ ቃሎች የሚረጋገጡበት ነው – ማቴ 24፡44-46፣ ሉቃ 21፡34-36፣ ሐዋ 1፡11

ለ. የክርስቲያኖች ተስፋ የሚጠናቀቅበት ነው ቲቶ 2፡13፣ ዮሐ 14፡1-5

ሐ. የክርስቲያኖች መጽናኛና የአለምን መከራ እንዲረሱ የሚያደርግ ነው – 1ተሰ 4፡14

ስለ ጌታ ዳግም ምፅዓት ስናስብ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች አብረን ማሰብ ወይም ማወቅ አለብን። ይኸውም ጌታ ለቅዱሳን ይመጣል የሚለውን 1ተሰ 4፡16-17 እና ከቅዱሳን ጋር ይመጣል የሚለውን ነው – ሐዋ 1፡11፣ ራዕ 1፡7፣ ማቴ 24፡29-31። የጌታችን አመጣጡ በአካላዊና ለሁሉም ሊታይ በሚችል አይነት ይገለጣል።

የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ፦ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ እንደሆነች የእግዚአብሔር ቃል ይመሰክራል – ራዕ 22፡17፣ 2ቆሮ 11፡1-2። ስለዚህ የእርሱ መገለጥ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደስታና የስራዋ መደምደሚያ ስለሆነ ለእርሷ የተለየ ጉዳይ ነው።

የመምጣቱ ምልክቶች ፦ የጌታ መምጣት ቀን ማንም እንደማያውቅ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል – ማቴ 24፡36፣ ማር 13፡32። ለመምጣቱ ምልክቶች በግልጽ ተቀምተዋል። ታላቅ የወንጌል ስርጭት ይካሄዳል – ማቴ 24፡14፣ በምድር ላይ ችግር፣ መከራና መናወጥ ይሆናል – ማቴ 24፡3-14፣ 2ጢሞ 3፡1-5። እስራኤል በታሪክ ከብዙህ ሺህ አመት በኋላ በመንግስት ደረጃ ትዋቀራለች – ኢሳ 11፡12፣ ሉቃ 21፡29

ታላቁ የመከራ ዘመን ፦ ከክርስቶስ ዳግም መምጣት በፊት ወይም ከቅዱሳን ንጥቀት በኋላ ሰባት የመከራ ዘመናት በምድር ላይ ይሆናሉ። ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ስለተነጠቀች የዚህ መከራ ተካፋይ አትሆንም – ራዕ 3፡20። በዚህ ዘመን አይሁዳውያን በተለየ ሁኔታ መንግስታቸውን ከሃሰተኛ መሲህ ጋር በመሆን ያጠነክራሉ። ቃል ኪዳንም ያደርጋሉ – ኢሳ 11፡11፣ ዳን 9፡27። የፈረሰውን ቤተ መቅደስ በመስራት አምልኳቸውን ያደርጋሉ – ዳን 9፡24፣ ማቴ 24፡ 15-22። በመጨረሻው የመከራ ዘመን ጌታ ይታደጋቸዋል። በእርሱም ይሆናሉ ለዘላለም – ዘካ 8፡13-23 አሞፅ 9፡15 ሕዝ 34፡28። በመጨረሻው የመከራ ዘመን ሁለት ነገር ይሆናል። ጌታ ለሺህ አመት ከቅዱሳን ካር መንገሱ – ማቴ 24፡29-30 እና ሰይጣን ለሺህ አመት መታሰር ይሆናል – ራዕ 20፡3

የሙታን ትንሳኤና የነጭ ዙፋን ፍርድ ፦ ይህ የሙታን ትንሳኤ የሚሆነው ከአንድ ሺህ አመት የምድር ጌታ አገዛዝ ካበቃ በኋላ ነው። በዚህ በነጭ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ጌታ ሲሆን በፊቱም የሚቆሙት በጌታ ሳያምኑ ሞተው የመጨረሻውን ፍርዳቸውን እንደስራቸው ለመቀበል ነው – ራዕ 20፡11-15። በጌታ ትንሳኤ መሃከል እና በቅዱሳን ትንሳኤ መሃከል እና በሙታን (በሃጢአተኞች) በሃከል አንድ ሺህ አመት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ ሰው አንድ ጊዜ ሞቶ ከዚያም በኋላ ስለሰራው ስራ የሚቀበለው ዋጋና ፍርድ እንደሚጠብቀው ያሳስበናል – ዕብ 9፡27።

የዘላለም ሕይወት ፦ በዘላለም ሕይወት ጅማሬ አሮጌው አልፎ አዲስ ነገር ይጀመራል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s