ስለዚህ ክርስቲያን ማን ነው?

መልስ 1፦ ዌብስተር መዝገበ ቃላት ክርስቲያን ማለት “በክርስቶስ የሚያምን ወይንም በክርስቶስ ትምህርት በተመሠረተ ሃይማኖት የሚያምን ሰው” ነው ሲል ያስቀምጠዋል። የክርስቲያን ምንነት ለመረዳት ይህ የዌብስተር ፍች መነሻ ሊሆነን ይችላል፤ ነገር ግን ልክ እንደሌሎቹ ዓለማዊ የሆኑ ፍችዎች ክርስቲያን መሆን የሚያመለክተውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ማስተላለፍ አይችልም።

ክርስቲያን የሚለው ቃል በሐዲስ ኪዳን ሦስት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኝዋለን (የሐዋርያት ሥራ ፲፩፥፳፮፤ የሐዋርያት ሥራ ፳፮፥፳፰፤ ፩ኛ ጴጥሮስ ፬፥፲፮)። የኢየሱስ ተከታዮች ክርስቲያን የሚል ስም በመጀመሪያ በአንጾኪያ ተሰጣቸው (የሐዋሪያት ሥራ ፲፩፥፳፮)፤ ይህም ስም የተሰጣቸው ሥራቸውና ጸባያቸው እንደክርስቶስ ስለነበር ነው። በመጀመሪያ ይህ ስም ያልዳኑት የአነጾኪያ ሰዎች ክርስቲያን የሆኑትን ላይ ለማላገጥ ያወጡላቸው ስም ነበር። ቀትተኛ ተርጉሙም፣ “የክርስቶስ ማኀበር አባል” ወይንም “የክርስቶስ ተከታይ” ማለት ነው።

ቢሆንም ከጊዜ በኋላ “ክርስቲያን” የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ አጥቶ የክርስቶስ ተከታይ ለሆነው ሳይሆን ግብረ ገባዊ በሆነ መንገድ ለሚመላለስ ማንኛውንም ሃይማኖተኛ የሚሰጥ ስም ሆኖ እናገኘዋለን። ብዙ ሰዎች በ ኢየሱስ ክርስቶስ ባያምኑም አንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመመላለሳቸው ወይንም “ክርስቲያን” በሆነ አገር በመኖራቸው ብቻ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ይሰይማሉ። ቢሆንም ግን ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ፣ ካነተ በታች የሆኑትን መርዳትና ጥሩ ሰው ሆኖ መገኘት ብቻ በራሱ ክርስቲያን አያደርግህም። አንድ ሰባኪ እንዳለው፣ “ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ አንድን ሰው ክርስቲያን አያደርገውም፤ ልክ ወደ ጋራዥ መመላለስ አንድን ሰው መኪና እንደማያደርገው ሁሉ።” የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን፣ ጉባኤ መከታተልና የቤተ ክርስቲያንን ሥራ መሥራት ብቻ ክርስቲያን አያደርግህም።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን የምንሠራው በጎ ሥራ ብቻውን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አያስገኝልንም። ቲቶ ፫፥፭ እነዲህ ይለናል፤ “ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው።” ስለዚህ፣ ክርስቲያን ማለት በእግዚአብሔር እንደገና የተወለደና (ዮሐንስ ፫፥፫፤ ዮሐንስ ፫፥፯፤ ፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥ ፳፫) እምነቱንም በክርስቶስ ያደረገ ሰው ነው። ኤፌሶን ፪፥፰ እነደሚለን፣ “በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከ እናንተ አይደለም።” እውነተኛው ክርስቲያን ለኀጢአቱ ንስሓ የገባና በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ያመነ ነው። እውነተኛ ክርስቲያኖች እምነታቸው ሃይማኖትን፣ ግብረ ገባዊ ሕጎችንና “አድርግ አታድርግ” ዝርዝሮችን ላይ አይደለም።

እውነተኛ ክርስቲያን እምነቱ በክርስቶስ ያደረገ፣ ክርስቶስ መስቀል ላይ የሞተው ለኀጢአታችን ሲል እነደሆነና በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነስቶ ሞት ላይ አቸናፊነቱን ያረጋገጠው በሱ ለሚያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለመስጠት መሆኑን ያመነ ማለት ነው። ዮሐንስ ፩፥፲፪ እንዲህ ይለናል፤ “ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ተሰጣቸው።” እውነተኛው ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባልና በክርሰቶስ አዲስ ሕይወት የተሰጠው ነው። የእውነተኛ ክርስቲያን መለያ ለሌሎች በሚያሳየው ፍቅርና ለእግዚአብሔር ቃል በሚያሳየው መታዘዝ ነው (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፬፤ ፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፲)።

በኢየሱስ ካመንኩ በኋላ የሚቀጥለው ርምጃ ምንድንው?

እነኳን ደስ ያለህ! ሕይወትን የሚቀይር ውሳኔ ነው የወሰንከው! “ቀጥሎስ?” ብለህ እየጠየቅክ ሊሆን ይችላል። “ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞዬን እንዴት እጀምራለሁ?” የሚል ጥያቄ ሊኖርህ ይችላል። ከዚህ በታች የተጠቀሱት አምስት መመሪያዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ፊና ይሰጡሃል።

፩. ድነት ምን ማለት እነደሆነ በደንብ መረዳትህን አረጋግጥ።

፩ኛ ዮሐንስ ፭፥፲፫ እነደሚለን፣ “በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ።” እግዚአብሔር ድነትን በደንብ እነዲገባን ይፈልጋል። ድነት እነዳለን ጽኑ እምነት እንዲኖረን እግዚአብሔር ይሻል። ባጭሩ፣ የድነት ቁልፍ ነጥቦች እነዚህ ናቸው፤

(ሀ) ሁላችንም ኀጥአን ነን። እግዚአብሔርን የሚያስቀይም ሥራም ሠርተናል (ሮሜ ፫፥ ፳፫)።

(ለ) ለኀጢአታችንም ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለዓለሙ መለያየት በተገባን ነበር (ሮሜ ፮፥፳፫)።

(ሐ) ኢየሱስ የኀጢአታችንን ዋጋ ለመቀበል መስቀል ላይ ሞተልን (ሮሜ ፭፥፰፤ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩)።

ይህ ነው እንግዲህ የድነት መልእክት! ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው ብለህ ካመንክ ትድናለህ! ኀጢአትህ ሁሉ እነደተሰርየልህና እግዚአብሔርም እነደማይርቅህ ቃል ገብቶልሃል (ሮሜ ፰፥፴፰-፴፱፤ ማቴዎስ ፳፰፥፳)። ድነትህ የተረጋገጠው በክርሰቶስ መሆኑ አትርሳ (ዮሐንስ ፲፥፳፰-፳፱)። በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ካመንክ፣ የዘለዓለም ሕይወትህ በሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ይሆናል!

፪. መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምር ጥሩ ቤተ ክርስትያን ፈልግ።

ስለ ቤተ ክርስቲያን ስታስብ ሕንጻውን አይደለም። ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡ ነው። የኢየሱስ አማኞች እርስ በራሳቸው ወገነኝነት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። ኢየሱስን ስለተቀበልክ፣ በምትኖርበት አጠገብ የሚገኝ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምን ቤተ ክርስቲያን ፈልገህ ቄሱን አነጋግር። በኢየሱስ ክርስቶስ ስላለህ እምነት አማክረው።

የቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ጥቅም መጽሐፍ ቅዱስ ለማስተማር ነው። የእግዚአብሔር መመሪያዎች ሕይወትህ ላይ እንዴት መተገበር እንደምትችል ትማራለህ። ጠንካራና የተሳካ ክርስቲያናዊ ኑሮ ለመምራት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ቁልፍ ነው። ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፫፥፲፮-፲፯ እንደሚለን፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።”

ሶስተኛው የቤተ ክርስቲያን ጥቅም ደግሞ ለአምልኮ ነው። አምልኮ ደግሞ ላደረገልን ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማድረስ ማለት ነው። እግዚአብሔር አድኖናል። እግዚአብሔር ይወደናል። እግዚአብሔር ያስብልናል። እግዚአብሔር መንገድ ይመራናል። ለዚህ ሁሉ ታድያ እነዴት አናመስግነው? እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ጻድቅ፣ ሩሩና ጸጋ የተሞላ ነው። ራእይ ፬፥፲፩ እንዲህ ያውጃል፣ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና።”

፫. ወደ እግዚአብሔር ትኩረት የምትሰጥበት በቀን የተወሰነ ጊዜ ይኑረህ።

በየቀኑ የተወሰነ ሰዓት ለእግዚአብሔር ትኩረት መስጠት አለብን። አንዳንድ ሰዎች ይህንን “የጸጥታ ሰዓት” ይሉታል። ሌሎቹ ደግሞ “ትጋት” ይሉታል፣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር በትጋት አተኩሮ መስጠታቸውን ለማስመልከት። ይህንን የአተኩሮ ጊዜ፣ አንዳንዶች ጠዋት ይመርጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከቀትር በኋላ። ይህንን ሰዓት ምን ስም ብንሰጠውም ሆነ በየተኛው የቀን ክፍለ ጊዜ ብናረገውም ወሳኝነት የለውም። ወሳኝ ሁኔታው ግን ከእግዚአብሔር ጋር የግል ሰዓት መለየታችን ነው። ይህ የግል ጊዜያችን ምን እናከናውንበታለን?

(ሀ) ጸሎት። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ንግግር ነው። ጭንቀትህም ሆነ ችግርህ ለእግዚአብሔር ንገረው። ጥበብና አመራር እንዲለግሥህ እግዚአብሔርን ጠይቀው። ፍላጎትህን እንዲያሟላልህ እግዚአብሔርን ጠይቀው። ምን ያህል እነደምታፈቅረውና እንደምታመሰግነው ንገረው። ጸሎት እንግዲህ ይህ ነው።

(ለ) የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ። በቤተ ክርስቲያን ወይንም በሰንበት ትምርህት ቤት ከምትማረው ውጪ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በግልህ ማንበብ አለብህ። ስኬታማ ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመምራት የሚያሰፈልጉህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ይዟል። ብልህ ውሳኔዎችን ለመወሰን፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ፣ ሌሎቹንን በደንብ ለማስተማርና በመንፈስ ለመበልጸግ የሚረዱንን የእግዚአብሔር መመሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ለኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወታችንን እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝና በሚያረካ መንገድ እንዴት መምራት እንዳለብን የሚያሳየን ከእግዚአብሔር የተሰጠን መምሪያ መጽሐፍ ነው።

(፬) በመንፈስ ሊያበረቱህ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት አጠንክር።

፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፥፴፫ እንደሚለን፣ “አትሳቱ፤ ‘መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”’ መጽሐፍ ቅዱስ “መጥፎ” ሰዎች ተጽዕኖ እንዳያሳድሩብን ያስጠነቅቀናል። ከእነዚህ አይነቶቹ ጋር መዋል በቀላሉ ሐጢአት ለመሥራት መገፋፋት ይሆናል፤ ምክኒያቱም ሲውል ሲያድር እነርሱን መምሰላችን አይቀርምና። ለዚህም ነው በእግዚአብሔር መንገድ ከሚመላለሱት ሰዎች ጋር ብቻ መዋል ያለብን።

ሊያበረታቱህ የሚችሉ አንድ ሁለት ሰዎች ከጉባኤህ ፈልግ (ዕብራውያን ፫፥፲፫፤ ፲፥፳፬)። ጓደኞችህን የጸጥታ ጊዜህን፣ የቀን ተቀን ተግባራትህንና ከእግዚአብሔር ጋር ለምታደርገው ጉዞህን እንዲከታተሉልህ ጠይቃቸው። አንተም በተራህ ይህንኑ እንድታደርግላቸው ጠይቃቸው። ከጓደኞችህ ጋር የምትካፈላቸውን አጋጣሚዎች እግዚአብሔር እንዲፈጥርልህ ጠይቀው።

፭. ተጠመቅ።

ጥምቀትን አስመልክቶ ብዙዎች የተሳሳተ አመለካከት አላቸው። “መጠመቅ” የሚለው ቃል ውኃ ውስጥ መነከርን ያመለክታል። ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መንገድ አዲሱ እምነትህን ለክርስቶስ ማወጅህንና ለሱ ራስህን ማስገዛትህን ያሳያል። ውኃ ውስጥ መነከር ከክርስቶስ ጋር መቀበርን ያመለክታል። ተነክረህ መውጣትህ ደግሞ የክርስቶስ ከሙታን መነሳትን ያመለክታል። ስለዚህም፣ መጠመቅ ከክርስቶስ መሞት፣ መቀበርና ከሙታን መነሳት ጋር መካፈልህን ያሳያል።

ጥምቀት አይደለም የሚያድንህ። ጥምቀት ከኀጢአትህ አያነጻህም። ጥምቀት በመሠረቱ በክርስቶስ ማመንህንና ለሱ መገዛትህን በአደባባይ የምታውጅበት ነው። ለመጠመቅ ዝግጁ ከሆንክ ቄስህን ወይም ፓስተርህን  አነጋግር።


Leave a comment